ሱራ Al-Qaari'a — The Calamity

ሱራ Al-Qaari'a (The Calamity) — 101/114 · 11 አንቀጾች. በአረብኛ ጽሑፍ እና በአማርኛ ትርጉም ያንብቡ እና ያዳምጡ።

ٱلۡقَارِعَةُ

ቆርቋሪይቱ (ጩኸት)፤

Ayah 1

مَا ٱلۡقَارِعَةُ

ምን አስደናቂ ቆርቋሪ ናት

Ayah 2

وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا ٱلۡقَارِعَةُ

ቆርቋሪይቱም ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ

Ayah 3

يَوۡمَ يَكُونُ ٱلنَّاسُ كَٱلۡفَرَاشِ ٱلۡمَبۡثُوثِ

ሰዎች እንደ ተበታተነ ቢራቢሮ (ወይም ኩብኩባ) በሚኾኑበት ቀን፤

Ayah 4

وَتَكُونُ ٱلۡجِبَالُ كَٱلۡعِهۡنِ ٱلۡمَنفُوشِ

ጋራዎችም እንደ ተነደፈ ሱፍ በሚኾኑበት (ቀን ልቦችን በድንጋጤ ትቆረቁራለች፡፡)

Ayah 5

فَأَمَّا مَن ثَقُلَتۡ مَوَٰزِينُهُۥ

ሚዛኖቹ የከበዱለት ሰውማ፤

Ayah 6

فَهُوَ فِي عِيشَةࣲ رَّاضِيَةࣲ‏

እርሱ በምትወደድ ኑሮ ውስጥ ይኾናል፡፡

Ayah 7

وَأَمَّا مَنۡ خَفَّتۡ مَوَٰزِينُهُۥ

ሚዛኖቹም የቀለሉበት ሰውማ፤

Ayah 8

فَأُمُّهُۥ هَاوِيَةࣱ‏

መኖሪያው ሃዊያህ ናት

Ayah 9

وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا هِيَهۡ

እርሷም ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ

Ayah 10

نَارٌ حَامِيَةُۢ

(እርሷ) በጣም ተኳሳ እሳት ናት፡፡

Ayah 11