ሱራ Al-Humaza — The Traducer

ሱራ Al-Humaza (The Traducer) — 104/114 · 9 አንቀጾች. በአረብኛ ጽሑፍ እና በአማርኛ ትርጉም ያንብቡ እና ያዳምጡ።

وَيۡلࣱ لِّكُلِّ هُمَزَةࣲ لُّمَزَةٍ

ለሃሜተኛ ለዘላፊ ሁሉ ወዮለት፡፡

Ayah 1

ٱلَّذِي جَمَعَ مَالࣰ ا وَعَدَّدَهُۥ

ለዚያ ገንዘብን የሰበሰበና የቆጣጠረው (ያደለበውም) ለኾነ ፤(ወዮለት)፡፡

Ayah 2

يَحۡسَبُ أَنَّ مَالَهُۥٓ أَخۡلَدَهُۥ

ገንዘቡ የሚያዘወትረው መኾኑን ያስባል፡፡

Ayah 3

كَلَّاۖ لَيُنۢبَذَنَّ فِي ٱلۡحُطَمَةِ

ይከልከል፤ በሰባሪይቱ (እሳት) ውስጥ በእርግጥ ይጣላል፡፡

Ayah 4

وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا ٱلۡحُطَمَةُ

ሰባሪይቱም ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ

Ayah 5

نَارُ ٱللَّهِ ٱلۡمُوقَدَةُ

የተነደደችው የአላህ እሳት ናት፡፡

Ayah 6

ٱلَّتِي تَطَّلِعُ عَلَى ٱلۡأَفۡـِٔدَةِ

ያቺ በልቦች ላይ የምትዘልቅ የኾነችው፡፡

Ayah 7

إِنَّهَا عَلَيۡهِم مُّؤۡصَدَةࣱ‏

እርሷ በእርግጥ በእነርሱ ላይ የተዘጋጀች ናት፡፡

Ayah 8

فِي عَمَدࣲ مُّمَدَّدَةِۭ

በተዘረጋች አዕማድ ውስጥ (የተዘጋች ናት)፡፡

Ayah 9