ሱራ At-Takaathur — Competition

ሱራ At-Takaathur (Competition) — 102/114 · 8 አንቀጾች. በአረብኛ ጽሑፍ እና በአማርኛ ትርጉም ያንብቡ እና ያዳምጡ።

أَلۡهَىٰكُمُ ٱلتَّكَاثُرُ

በብዛት መፎካከር (ጌታችሁን ከመገዛት) አዘነጋችሁ፡፡

Ayah 1

حَتَّىٰ زُرۡتُمُ ٱلۡمَقَابِرَ

መቃብሮችን እስከ ጎበኛችሁ ድረስ፡፡

Ayah 2

كَلَّا سَوۡفَ تَعۡلَمُونَ

ተከልከሉ፤ ወደፊት (ውጤቱን) ታውቃላችሁ፡፡

Ayah 3

ثُمَّ كَلَّا سَوۡفَ تَعۡلَمُونَ

ከዚያም ተከልከሉ፤ ወደ ፊት ታውቃላችሁ፡፡

Ayah 4

كَلَّا لَوۡ تَعۡلَمُونَ عِلۡمَ ٱلۡيَقِينِ

በእውነቱ (የሚጠብቃችሁን) እርግጠኛ ዕውቀትን ብታውቁ ኖሮ፤ (ባልዘናጋችሁ ነበር)፡፡

Ayah 5

لَتَرَوُنَّ ٱلۡجَحِيمَ

ገሀነምን በእርግጥ ታያላችሁ፡፡

Ayah 6

ثُمَّ لَتَرَوُنَّهَا عَيۡنَ ٱلۡيَقِينِ

ከዚያም እርግጠኛን ማየት ታዩዋታላችሁ፡፡

Ayah 7

ثُمَّ لَتُسۡـَٔلُنَّ يَوۡمَئِذٍ عَنِ ٱلنَّعِيمِ

ከዚያም ከድሎታችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ፡፡

Ayah 8