ሱራ Al-Aadiyaat — The Chargers

ሱራ Al-Aadiyaat (The Chargers) — 100/114 · 11 አንቀጾች. በአረብኛ ጽሑፍ እና በአማርኛ ትርጉም ያንብቡ እና ያዳምጡ።

وَٱلۡعَٰدِيَٰتِ ضَبۡحࣰ ا

እያለከለኩ ሩዋጮች በኾኑት (ፈረሶች) እምላለሁ፡፡

Ayah 1

فَٱلۡمُورِيَٰتِ قَدۡحࣰ ا

(በሰኮናቸው) እያጋጩ እሳትን አውጪዎች በኾኑትም፤

Ayah 2

فَٱلۡمُغِيرَٰتِ صُبۡحࣰ ا

በማለዳ ወራሪዎች በኾኑትም፤

Ayah 3

فَأَثَرۡنَ بِهِۦ نَقۡعࣰ ا

በእርሱ አቧራን በቀሰቀሱትም፤

Ayah 4

فَوَسَطۡنَ بِهِۦ جَمۡعًا

በ(ጠላት) ክቢ መካከል በእርሱ (በጧት) በተጋፈጡትም እምላለሁ፡፡

Ayah 5

إِنَّ ٱلۡإِنسَٰنَ لِرَبِّهِۦ لَكَنُودࣱ‏

ሰው ለጌታው ብርቱ ከሓዲ ነው፡፡

Ayah 6

وَإِنَّهُۥ عَلَىٰ ذَٰلِكَ لَشَهِيدࣱ‏

እርሱም በዚህ ላይ መስካሪ ነው፡፡

Ayah 7

وَإِنَّهُۥ لِحُبِّ ٱلۡخَيۡرِ لَشَدِيدٌ

እርሱም ገንዘብን ለመውደድ በጣም ብርቱ ነው፡፡

Ayah 8

۞أَفَلَا يَعۡلَمُ إِذَا بُعۡثِرَ مَا فِي ٱلۡقُبُورِ

(ሰው) አያውቅምን? በመቃብሮች ያሉት (ሙታን) በተቀሰቀሱ ጊዜ፤

Ayah 9

وَحُصِّلَ مَا فِي ٱلصُّدُورِ

በልቦች ውስጥ ያለውም ሁሉ በተገለጸ ጊዜ (እንዴት እንደሚኾን)፡፡

Ayah 10

إِنَّ رَبَّهُم بِهِمۡ يَوۡمَئِذࣲ لَّخَبِيرُۢ

ጌታቸው በዚያ ቀን በእነርሱ (ነገር) በእርግጥ ውስጠ አዋቂ ነው፡፡

Ayah 11